Search
Close this search box.

በገቢ ሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት ተደረገ

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ከክልሉ እና ከባህርዳር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ከመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የገቢ ሪፎርም ስራዎችን በሚመለከት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡

የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ

በአማራ ክልል ለሚገኙ የደረጃ “ሀ” ደረጃ “ለ” እና ደረጃ “ሐ” የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 15/2015 ዓ.ም ንዑስ አንቀፅ 6 መሠረት የቤት ኪራይ ገቢ ግብርን በግምት ለመወሰን የሚከተሉት መልዕክቶች ትኩረት መስጠት ይገባል።

ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ የተደረጉ ዕቃዎች

ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ዕቃዎች፣ የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግርን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል እንዲሁም ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ ይጣላል፡፡ ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ ከተደረጉ እቃዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ለማየት read more የሚለውን በመጫን ማየት ይቻላል።

የብረታብረት፣ የአውቶሞቲቭ እና “ኢንደስትሪያል” ዘይቶችና ቅባቶች ወደ አገር ሲገቡም ሆነ በአገር ውስጥ ሲሸጡ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚሰበሰብባቸው ያውቁ ይሆንን?

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴርን ደብዳቤና ቁጥር ጠቅሶ ለመምሪያዎች ባስተላለፈው መልዕክት የሚኒስቴሩ ደብዳቤ ከወጣበት መጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም በፊት የተገባን የአቅርቦት ውል ሳይጨምር የብረታ ብረት፣ የአውቶሞቲቭ እና ኢንደስትሪያል ዘይቶችና ቅባቶች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ ምርቶች በአገር ውስጥ ሲሸጡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሊሰበሰብ የሚገባ መሆኑን እና ከተጠቀሰው ቀን በፊት የተጻፉ ማስፈፀምያ ደብዳቤዎች እና እነሱን መሠረት ያደረጉ ደብዳቤዎች በአዲስ የተተኩ መሆኑን አሳውቋል።

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ እነኚህን ተግባራት እንዳያደርጉ

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚ የሆኑ ግብር ከፋዮች ፈጽሞ ማድረግ የሌለባቸው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው በጥገና ላይ ባለበት ጊዜ ካልሆነ በስተቀር በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ከታተመ ደረሰኝ ውጭ ሌላ ማንኛውንም ዓይነት ደረሰኝ መሰጠት….