በአማራ ክልል ለሚገኙ የደረጃ “ሀ” ደረጃ “ለ” እና ደረጃ “ሐ” የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 15/2015 ዓ.ም ንዑስ አንቀፅ 6 መሠረት የቤት ኪራይ ገቢ ግብርን በግምት ለመወሰን የሚከተሉት መልዕክቶች ትኩረት መስጠት ይገባል።
1. በአከራይና በተከራይ መካከል የተፈፀመ የኪራይ ውል ስምምነት የገንዘብ መጠን ትክክለኛነቱ በገቢ ተቀባይነት ካገኘ በውል ስምመነቱ መሠረት ግብር ይወሰናል፣
2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሁኖ ከሦስተኛ ወገን የተገኘ የግብይት መረጃው የግዥ መረጃ ከሆነ ወደ ሽያጭ መቀየር ይኖርበታል።
3. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 መሠረት መወሰን ካልተቻለ በአዋጁ አንቀፅ 3 መሠረት ወቅታዊ ትክክለኛ የኪራይ ዋጋ ጥናት ተወስዶ የግብር ስሌቱ የሚሰራ ይሆናል።
4. የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋይ በሚሰላበት ጊዜ ከግብር ዓመቱ ጠቅላላየኪራይ ገቢው ውስጥ ለቤቶቹ፣ ለቤት ዕቃና መሳሪያማደሻ መጠገኛ ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከኪራዩ ጠቅላላ ገንዘብ ለይ እንደ ወጪ 50% ተይዞ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ “ለ” መሠረት ይሰላል።
5. አከራይ ከአንድ ዓመት በላይ የሚሸፍን የኪራይ ክፍያ የተቀበለ እንደሆነ የኪራይ ገቢው በግብር ዘመኑ ተጠቃሎ ተይዞለት ግብሩ ገቢው ለሚሸፍናቸው ዓመታት ተሸንሽኖ በዚህ አንቀፅ በንዑስ አንቀፅ 4 በተመለከተው መጣኔ መሠረት እንዲከፈል ይደረጋል።
6. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 5 በተመለከተው መንገድ ከአንድ ዓመት በላይ የሚቆይ የኪራይ ውል የውል ዘመኑ ከማለቁ በፊት የተቆረጠ እንደሆነና ለተከራዩ ቀሪ ክፍያ መመለሱ በማስረጃ ሲረጋገጥ በብልጫ የከፈለው ተሰልቶ ሊመለስለት ወይም ለቀጣይ የግብር ዘመን ታክስ ከፋዩ በጽሁፍ ሲረጋገጥ በብልጫ የከፈለው ተሰልቶ ሊመለስለት ወይም ለቀጣይ የግብር ዘመን ታክስ ከፋዩ በጽሁፍ ፍላጎቱን ሲገልፅ በታሳቢነት እንደሚያዝለት መመሪያው ያመላክታል።