የባ/ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የ8 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ማለትም ከ ሀምሌ 01 /2015 እስከ የካቲት 30/2016 ከታቀደዉ ከመደበኛ ገቢ ብር 2,140,565,416.21 (40.12%) እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 479,919,306.24(15.10%) በድምሩ 2,620,484,722.5(30.78%) ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡
በገቢ ሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት ተደረገ
በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ከክልሉ እና ከባህርዳር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ከመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የገቢ ሪፎርም ስራዎችን በሚመለከት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡