የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ እነኚህን ተግባራት እንዳያደርጉ
- የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው በጥገና ላይ ባለበት ጊዜ ካልሆነ በስተቀር በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ከታተመ ደረሰኝ ውጭ ሌላ ማንኛውንም ዓይነት ደረሰኝ መሰጠት፣
- ከተመዘገበ የአገልግሎት ማዕከል ጋር ውል ሰይፈራረሙ የንግድ ስራ ማከናወን፣
- ዕውቅና ያልተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ ተጠቅሞ የንግድ ስራ ማከናወን፣
- በቢሮው ያልተመዘገበ የሽያጭ መመዝገቢያ ተጠቅሞ የንግድ ስራ ማከናወን፣
- የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን ከተርሚናል ጋር ሳያይዙ የንግድ ስራ ማከናወን፣
- ለቢሮው ሳያሳውቁ የአድራሻ ወይም የስም ለውጥ ማድረግ፣
- ዕቃዎቹ ተመላሽ መደረጋቸው ወይም ደንበኛው የተመላሽ ጥያቄ ማቅረቡ በተመላሽ መዝገብ ላይ በትክክል መመዝገቡ ሳይረጋገጥ የተመላሽ ደረሰኝ መስጠት፣
- የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው በሥርቆት ወይንም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ አገልግሎት መስጠት ሲያቋርጥ በሦስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ይህንኑ ለቢሮው ያለማሳወቅ፣
- የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው ብልሽት ባጋጠመው በ2 ስዓት ጊዜ ውስጥ ለመሣሪያ አገልግሎት ለቢሮው /በአቅራቢያዎ ለሚገኝ መምሪያ/ ሪፖርት ያለማድረግ፣
- የምርመራው መዝገብ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው ጎን እንዲቀመጥ ያለማድረግ፣
- በቢሮው ሠራተኛ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዉን ሥርዓት ኦዲት እንዳያደረግ መሰናክል መፍጠር፣
- በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው የፊሲካል ማሸጊያ ላይ ጉዳት ማድረስ ወይንም መቀየር፣
- እንዲሁም በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው ላይ በዓመት አንድ ጊዜ የቴክኒክ ምርመራ በተዋዋለው የመሣሪያ አገልግሎት ማዕከል ያለማድረግ የተከለከለ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ተግባራት ፈጽሞ መገኘት በግብር ህጎች ድንጋጌዎች መሠረት የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡
ስለዚህ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ አውቀው እንዲተገብሩ እናሳስባለን
ከአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ቴሌግራም የተወሰደ