Search
Close this search box.

በገቢ ሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት ተደረገ

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ከክልሉ እና ከባህርዳር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ከመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የገቢ ሪፎርም ስራዎችን በሚመለከት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ከክልሉ እና ከባህርዳር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ከመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የገቢ ሪፎርም ስራዎችን በሚመለከት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡

የከተሞች ገቢ ሪፎርም ስራዎችን በፕሮጀክቱ ናሙና ከተማ በሆነችው የባህርዳር ከተማ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ለመተግበር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዚነት ኢብራሂም እንደገለጹት የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት እየሰራቸው ባሉ የሪፎርም ስራዎች በከተሞች የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣ መሆኑን ገልጸው የሪፎርም ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው የክልልና የከተማ አመራሮች ትልቁን ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማም በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተጠንተው የተለዩ ከፍተኛ የመዘጋጃ ቤታዊ የገቢ ምንጭ የሚሆኑትን የገቢ አይነቶች የጥናት ግኝትና የትግበራ ስልቶች ላይ በጥልቅ በመወያየት ጥናቶቹን ሙሉ በሙሉ በክልሉ እና በከተሞች በማስፋት የነዋሪዎችን የልማት ፍላጎት በራሳቸው ማሳካት እንዲችሉ ውይይቱ ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በእለቱ የፋይናንስ ስትራቴጂ ሰነድ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ልየታ፣ በጂ.አይ.ኤስ ካርታ ማስፈርና ግመታ ጥናት፣ የንብረት ግመታ አዋጅ እና ዋና ዋና ገጽታዎች፣ የከተማ ንግድ አገልግሎት ክፍያ ጥናት፣ የመንገድ ተጠቃሚዎች ክፍያ ጥናት፣ በለማው የንብረት ግብር ስርዓት እና ሪፎርሙን ለመተግበር የአመራሩ ሚና ምን መምሰል አለበት በሚሉ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱሌማን እሸቱ እና የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ደጀኔ ውይይቱ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ባላቸው የገቢ ምንጭ የራሳቸውን ወጪዎች እንዲሸፍኑ ከማድረጉም በላይ ዘመናዊ የግብር አከፋፈል ስርዓትን የተከተለ ውይይት በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል፤ ይህንንም ወደ ሌሎች ከተሞች በማስፋት በተግባር ላይ ለማዋል እንሰራለን በማለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ይህንን የውይይት መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

መረጃው የኢፌዴሪ ከተሞችና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ነው::

Share:

More Posts

የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ

በአማራ ክልል ለሚገኙ የደረጃ “ሀ” ደረጃ “ለ” እና ደረጃ “ሐ” የንግድ ስራ እና የኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 15/2015 ዓ.ም ንዑስ አንቀፅ 6 መሠረት የቤት ኪራይ ገቢ ግብርን በግምት ለመወሰን የሚከተሉት መልዕክቶች ትኩረት መስጠት ይገባል።

ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ የተደረጉ ዕቃዎች

ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ዕቃዎች፣ የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግርን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል እንዲሁም ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ ይጣላል፡፡ ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ ከተደረጉ እቃዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ለማየት read more የሚለውን በመጫን ማየት ይቻላል።

Send Us A Message