ግብር አግባብነት ባላቸው ህጎች በመንግስት የሚጣል ከመሆኑም በላይ ግብር ለስልጣኔ የሚከፈል ዋጋ ነው።
በመሆኑም ግብር በየትኛውም አለም የሚፈፀም ኩነት መሆኑን በመረዳት በክልላችን ብሎም የክልሉ ዋና መዲና በሆነችው ዋና ከተማ የሚኖሩ ወደግብር ከፋዮችም ግብር በመክፈል አገራዊና ክልላዊ ለሚኖሩባት ከተማ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግር መፍቻ መንገድ ብቻ ሳይሆን የከተማውን መሰረት ልማት ለማልማት ዋና መስሪያ መሆኑን በመገንዘብ የባህር ዳር ግብር ከፋዮች ግብርን የመክፍል ልምድ አስገዳጅና በጫና ሳይሆን ለስልጣኔ የሚከፈል መሆኑን በመረዳት የሚከፍል፣ ህግ አክባሪ፣ ዘመናዊ፣ ለአገሩና ለወገኑ እድገት ተቆርቋሪ መሆኑን እስከአሁን በመጣንበት “ግብር በራሱ ተነሳሽነት” በመክፈል ወገናዊነትን አሳይቷል። ይህ የባህርዳር ነጋዴ ግብር ከፋይ የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን ማሳያ ነው።